On this page
እራስዎን እና ሌሎችን ከኮቪድ-19 ይከላከሉ
ኮቪድ-19 አሁንም በህብረተሰቡ ውስጥ እየተሰራጨ ነው። አሁንም አንዳንድ ሰዎችን በጣም ሊያሳምም ይችላል። ራስን መከላከል ሌሎችን ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው። ኮቪድ ካልያዝዎት ኮቪድን ማሰራጨት አይችሉም።
ይመርመሩ
እንደሚከተለው ከሆነ፣ ቤት ይቆዩ እና ፈጣን አንቲጂን ምርመራ (RAT) ያድርጉ፦
- እንደ ንፍጥ፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ ሳል፣ ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት ያሉ ምልክቶች ካለዎት።
- ኮቪድ-19 ያለበት አንድ ሰው ጋር ግንኙነት ያለዎት ከሆኑ።
የምርመራ ውጤትዎ የለም (ነጋቲቭ) የሚል ከሆነ፣ ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ፈጣን አንቲጂን ምርመራዎችን ይጠቀሙ እና የሕመም ምልክቶችዎ እስኪወገዱ ድረስ በቤት ውስጥ ይቆዩ።
በኮቪድ-19 በጣም ከታመሙ፣ የፒሲአር (PCR) ምርመራ እንዲደረግልዎት ሃኪም (GP) ይጠይቁ። ከፒሲአር (PCR) ምርመራ አለው (ፖዘቲቭ) የሚል የምርመራ ውጤት ካገኙ፣ ውጤቱን ሪፖርት ማድረግ አያስፈልግዎትም።
የኮቪድ-19 ምርመራን ያግኙ በሚለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ጤናዎን ይጠብቁ
የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤትዎ አለው (ፖዘቲቭ) የሚል ከሆነ፣ እረፍት ማድረግ ብሎም ሐኪም ማነጋገር አለብዎት። ብዙ ሰዎች ቀለል ያሉ ምልክቶች ይኖራቸዋል እናም በቤት ውስጥ ሊያገግሙ ይችላሉ። የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፦
- ቢያንስ ለ 5 ቀናት በቤት ውስጥ ይቆዩ። ወደ ሥራ ወይም ወደ ትምህርት ቤት አይሂዱ። ከሆስፒታሎች፣ ከአረጋውያን እንክብካቤ መስጫ ተቋማት እና ከአካል ጉዳት አገልግሎቶች ይራቁ።
- በድንገተኛ ጊዜ ከቤት መውጣት ካለብዎት የአፍ እና የፊት ጭምብል ያድርጉ። በጣም ጥሩ ጭምብሎች የቀዶ ጥገና ወይም N95 ናቸው።
- ያገኟቸውን ሰዎች ወይም በቅርብ ጊዜ የሄዱባቸውን ቦታዎች ኮቪድ እንዳለብዎት ይንገሩ።
ምልክቶችዎ እየተባባሱ ከሄዱ፣ ሓኪም (GP) ማነጋገር አለብዎት።
ሃኪም (GP) ማነጋገር ካልቻሉ ለአስቸኳይ እንክብካቤ ወደ ቪክቶሪያ ምናባዊ ድንገተኛ ክፍል (Virtual Emergency Department) ይደውሉ።
ለአደጋ ጊዜ ሶስት ዜሮ (000) ይደውሉ።
እስከ 10 ቀናት ድረስ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ንፍጥ፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ላብ ወይም የትንፋሽ ማጠር ካለብዎ ቤት መቆየት አለብዎት። እርግጠኛ ካልሆኑ ፈጣን አንቲጂን ምርመራ ይጠቀሙ ወይም ሃኪም (GP) ያነጋግሩ።
ድጋፍ
ለበለጠ መረጃ፦
- በኮቪድ-19 መያዝዎን ካረጋገጡ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ለማወቅ የኮቪድ-19 የማረጋገጫ ዝርዝርን ይጎብኙ።
- ለህመም ምልክቶች እና ጤናዎን እቤት ውስጥ ለመንከባከብ የኮቪድ-19 አስተዳደርን ይጎብኙ።
ከሆነ ሰው ጋር ለመነጋገር፡-
- የትርጉም እና የአስተርጓሚ አገልግሎትን በ 131 450 ይደውሉ
ስለ ኮቪድ መድሃኒቶች ይጠይቁ
የኮቪድ መድሃኒቶች ህይወትን ያድናሉ፤ እንዲሁም ሰዎች በኮቪድ-19 በጣም እንዳይታመሙ ያደርጋሉ። በተሻለ ሁኔታ እንዲሰሩ፣ በተሻለ ፍጥነት መወሰድ አለባቸው፤ ከታመሙ በኋላ በ 5 ቀናት ውስጥ።
ለኮቪድ መድሃኒቶች ብቁ መሆንዎን ለማወቅ እነዚህን ጥያቄዎች ይመልሱ። ብቁ ነኝ ብለው ካሰቡ ሃኪም (GP) ያነጋግሩ። ብቁ የሆኑ ሰዎች በፍጥነት ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ሃኪም (GP) መርዳት ይችላል።
ለበለጠ መረጃ ፀረ-ቫይረስ እና ሌሎች መድሃኒቶችን ይመልከቱ።
የአፍ እና የአፍንጫ ጭምብል ያድርጉ
የአፍ እና የአፍንጫ ጭንብሎች በኮቪድ-19 እንዳይያዙ እና እንዳያሰራጩ ሊያግዙ ይችላሉ። የአፍ እና የአፍንጫ ጭምብሎች ጥሩ ጥራት ያላቸው እና ፊትን በደንብ የሚገጥሙ መሆን አለባቸው። N95 እና P2 የአፍ እና የአፍንጫ ጭምብሎች (መተንፈሻ) ከፍተኛውን ጥበቃ ይሰጣሉ።
የአፍ እና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ አለብዎት፦
- በሕዝብ መጓጓዣ፣ በሕዝብ ቦታዎች ውስጥ፣ እና ውጪ በሕዝብ በተጨናነቀ ቦታ።
- ኮቪድ-19 ካለዎት እና ከቤት መውጣት ካለብዎት
- እርስዎ በጣም ለመታመም በከፍተኛ አደጋ ላይ ከሆኑ፤ ወይም በከባድ ለመታመም ከፍተኛ አደጋ ላይ ካለ ሰው ጋር ከሆኑ።
ዕድሜያቸው 2 ዓመት ወይም ከዚያ በታች የሆኑ ህጻናት የመታፈን እና የመታነቅ አደጋ ስለሚኖረው የአፍ እና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ የለባቸውም።
ለበለጠ መረጃ የፊት ጭንብሎችን ይመልከቱ።
የሚቀጥለውን የክትባት መጠን ይውሰዱ
ክትባት እራስዎን እና ቤተሰብዎን በኮቪድ-19 በጣም ከመታመም ለመከላከል ምርጥ መንገድ ነው። ለእርስዎ የተፈቀዱ/የተመከሩ ክትባቶች በወቅቱ በመውሰድ ሁሉንም አሟልተው መገኘት አለብዎት። ለእርስዎ ምን ያህል መጠን እንደሚመከር ለማወቅ ሃኪሙን (GP) ያነጋግሩ።
ኮቪድ-19 ከዚህ በፊት ተይዘው የነበረ ቢሆንም አሁንም መከተብ አለብዎት። የሚቀጥለውን መጠንዎን ሃኪም ጋር ወይም በአካባቢ ፋርማሲ ውስጥ ለማስያዝ የክትባት ክሊኒክ ጠቋሚ ይጠቀሙ።
ለበለጠ መረጃ የኮቪድ-19 ክትባትን ይመልከቱ።
ንጹህ አየር ወደ ውስጥ እንዲገባ ይፍቀዱ
ኮቪድ-19 የሚተላለፈው በአየር ላይ ነው። ንጹህ አየር ወደ ቤት ውስጥ እንዲገባ ማድረግ የኮቪድ-19 ስርጭት ስጋት ይቀንሳል። ከቤት ውስጥ ከሌሎች ጋር በሚሰበሰቡበት ጊዜ መስኮቶችን ወይም በሮችን ይክፈቱ። ካልቻሉ የኤሮሶል ቅንጣቶችን ከአየር ላይ የሚያስወግድ ተንቀሳቃሽ የአየር ማጽጃ (HEPA filter) መጠቀም ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ የአየር ማናፈሻን ይመልከቱ።
ከኮቪድ-19 ማገገም
ብዙ ሰዎች አስተላላፊ መሆን ካበቁ በኋላ የኮቪድ-19 ህመም ይሰማቸዋል። ሰውነትዎ በትክክል ማገገም እንዲችል ጊዜ እና እንክብካቤ ይፍቀዱለት።
የሚቀጥለውን የክትባት መጠን ከመከተብዎ በፊት በበሽታው ከተያዙ በኋላ ለ 6 ወራት ያህል መጠበቅ አለብዎት። ይህ ከቫይረሱ የተሻለውን መከላከያ እንዲያገኙ ያረጋግጣል።
ካገገሙ ከ4 ሳምንታት በኋላ በኮቪድ-19 እንደገና ሊያዙ ይችላሉ። በበሽታው ከተያዙ ከ 4 ሳምንታት ወይም ከዚያ በኋላ ምልክቶች ካሉዎት ምርመራ ማድረግ አለብዎት።
ረጅም ኮቪድ (Long COVID) የሚባለው የኮቪድ-19 ምልክቶች ከ3 ወራት በላይ በሚቆዩበት ጊዜ ነው። የሕመም ምልክቶችዎን ለመቆጣጠር የሚረዳዎትን ወይም አስፈላጊ ከሆነ ወደ ልዩ ባለሙያ ሥልጣን በላይ እንዲባሉ ሊረዳዎት የሚችለውን ዶክተር ማየት አለብዎት።
በረጅም ኮቪድ (Long COVID) ላይ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።
በሽታው ከያዘው ሰው ጋር ግንኙነት የነበርዎት ከሆኑ
አለው (ፖዘቲቭ) የሚል የምርመራ ውጤት ካገኘ አንድ ሰው ጋር ቤት የሚጋሩ ከሆነ ወይም የቅርብ ግንኙነት ካደረጉ በኮቪድ-19 የመያዝ አደጋ ላይ ነዎት።
አለው (ፖዘቲቭ) የሚል የምርመራ ውጤት ካገኘ አንድ ሰው ጋር ከተገናኙ በኋላ ምልክቶቹን መከታተል እና ለ 7 ቀናት በመደበኛነት መመርመር አለብዎት። በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚከተለውን እንዲያደርጉ ይመከራል፦
- ከሆስፒታሎች፣ ከአረጋውያን የእንክብካቤ መስጫ ተቋማት እና ከአካል ጉዳተኛ አገልግሎቶች ይራቁ
- ከቤት ሲወጡ እና በሕዝብ ማመላለሻ ውስጥ እና እንደ ሥራ እና ትምህርት ቤት ባሉ የቤት ውስጥ ቦታዎችን ሲሆኑ የአፍ እና የአፍንጫ ጭንብል ያድርጉ
- በተቻለ መጠን መስኮቶችን በመክፈት ንጹህ አየር ወደ ቤት ውስጥ ቦታዎች እንዲገባ ያድርጉ
ለበለጠ መረጃ በሽታ ከያዘው ጋር ግንኙነት ላላቸው ማረጋገጫ ዝርዝር ይመልከቱ።